Description
ይህ የ”ምስክሮች” ተከታታይ የግጥም መጽሐፍ ሦስተኛ ክፍል ነው።
አስቀድማ በልደቱ ወቅት በበረት ውስጥ ትንፋሿን በመስጠት አምላኳን ስታገለግል እና ልጇን ስታስተምር የነበረችው አህያ እንደዚሁም ወደ ግብፅ ሲሰደድ የትህትና እናት የሆነችውን እመቤታችንን ጨምሮ በጀርባዋ ተሸክማ በረሃ ለበረሃ አብራቸው ተንከራታለች :: በዚህ በቁጥር ሦስት መጽሐፍ ደግሞ በልደቱ ሕፃን የነበረችው አህያ በዚህ መጽሐፍ ላይ እናት ሆና ከልጇ ጋር በልሳነ ሰብዕ እየተነጋገሩ ከእናትዋ የተማረቸውን እና ያየችውን ስለ ሆሣዕና ምስክርነቷን ትሰጣለች ለልጇም ታስተምራለች።
ይህን መጽሐፍ ከሌሎች የግጥም መጻሕፍት ልዩ የሚያደርገው፡
ልዩ ምስክሮች፦ እንስሳት እና ግኡዛን ፍጥረታት መሆናቸው
የታሪክ ቅብብሎሽ፦ በክፍል አንድ እና ሁለት ምስክርነት ስትሰጥ የበረቸው አህያ ልጅ በሦስተኛ ክፍል እናት ሆና ታሪኩን ለልጇ እያስተማረች ትቀጥላለች።
ሁለት ቋንቋ፦ መጽሐፉ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች መዘጋጀቱ
ግጥም፦ ታሪኩ ሙሉውን በግጥም መልክ መዘጋጀቱ
አስተማሪነት፦ ለቤተሰብ፣ ለሰንበት ት/ቤቶች እና በላይብረሪ ውስጥ ለጥቅም እንዲውል ታስቦ መዘጋጀቱ









Reviews
There are no reviews yet.